መዝሙረ ዳዊት በግእዝ እና አማርኛ | PSALMS

መዝሙረ ዳዊት በግእዝ እና አማርኛ | PSALMS

An application that contains the complete Psalm reading in Geez and Amharic

App info


1.2
October 05, 2024
Everyone
Get መዝሙረ ዳዊት በግእዝ እና አማርኛ | PSALMS for Free on Google Play

Advertisement

App description


Android App Analysis and Review: መዝሙረ ዳዊት በግእዝ እና አማርኛ | PSALMS, Developed by Nigat Systems. Listed in Books & reference Category. Current Version Is 1.2, Updated On 05/10/2024 . According to users reviews on Google Play: መዝሙረ ዳዊት በግእዝ እና አማርኛ | PSALMS. Achieved Over 119 thousand Installs. መዝሙረ ዳዊት በግእዝ እና አማርኛ | PSALMS Currently Has 4 thousand Reviews, Average Rating 4.7 Stars

መዝሙረ ዳዊት ለቤተክርስቲያን እና ለግል ጸሎት እጅግ የተወደደ ለሐዘን ለደስታ ለመልካምም ሆነ ክፉ ለማንኛውም ሁኔታ የሚያመሰግኑበት ፡ የሚጸልዩበት ፡ የመዝሙር እና የጸሎት መጽሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ እየተጠቀመ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሊገናኝ ፡ ኅብረቱም ሊያድግ በመንፈሳዊነትም ሊያድግ ይችላል።
መዝሙረ ዳዊት አጠቃላይ መዝሙሩ 150 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 82 ቱ የዳዊት መሆኑ ተገልጿል የቀረው የሙሴና የቆሬ የአሳፍ የሐጌና ዘካርያስ የሚሉና ደራሲው ያልታወቀ ይገኝበታል ።

መዝሙሮቹ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተገለጡ ጸሎትና ውዳሴ ናቸው። ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ኅብረት የሰውን ጥልቅ የልብ ስሜት ይገልጻሉ እነርሱም መታመንን ፤ ፍቅርን ፤ ልዕልናን ፤ ምስጋናንና ውዳሴን ፤ ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ኅብረት እንዲኖርመናፈቅን እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግን ፤ ከበደል ነጻ እንዲሆን መጠየቅን ፤ ከእግዚአብሔር ትድግና ለማግኘት መማጸንን ውዳሴውና ምስጋናው እግዚአብሔር በማንነቱ ስለደረገው ታላቅና ድንቅ ነገር ሁሉ ለማመስገን ነው። አንዳንዶቹ መዝሙሮች ስለመሲሑ ዋና ዋና የሆኑትን ክፍሎች ይዘው ይገኛሉ።

መዝሙረ ዳዊት የሰውን ይህይወት ዘመን ሳይለይ ሰው በሕይወቱ የሚያጋጥሙትን ኃዘንና ደስታ ፡ መልካምና ክፉ ፡ መውደቅና መነሣት ፡ ችግርና ምቾት ፡ ከእግዚአብሔር መራቅና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የያዘ መጽሐፍ ነው።

ለቤተክርስቲያን የጸሎትና የመዝሙር መጻሕፍት መሠረታቸው መዝሙረ ዳዊት ነው። መዝሙረ ዳዊት መዘምራን በዜማ ስልት የሚገለገሉበት መነኮሳት እና ካህናት በመዓልት በሌሊት በቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ፡ ምእመናን በያሉበት ሆነው እየጸለዩ መላእክተ ብርሃንን የሚያቀርቡበት ፡ መላእክተ ጽልመትን የሚያርቁበት ፡ ሕሙማን የሚፈወሱበት እጅግ ጠቃሚ የሆነው መጽሐፍ ነው።
መዝሙረ ዳዊት ሰዎች በዚህች ዓለም በሚኖሩበት ጊዜ ስለ ሚያጋጥሟቸው ሁኔታዎች በሙሉ ምን መጸለይ እንደሚገባቸው የሚያስረዳ መጽሐፍ ስለሆነ ከዚህ ቀጥሎ እንደቀረበው የመጽሐፉን አብዛኛውን ይዘት መረዳት ይቻላል፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ
መዝ.፰፣ መዝ.፳፱፣ መዝ.፴፫ መዝ.፴፮፣ መዝ.፹፱፣ መዝ.፺፬፣ መዝ.፩፻፫፣ መዝ.፩፻፬፣ መዝ.፩፻፭፣ መዝ.፩፻፮፣ መዝ. ፩፻፲፩፣ መዝ. ፩፻፲፰፣ መዝ.፩፻፴፰፣ መዝ.፩፻፵፭፡፡

የእግዚአብሔርን የባሕርይ ልዕልና ለመግለጥና ለማወደስ
መዝሙር ፰፣ ፲፱፣ ፳፱፣ ፴፫፣ ፵፯፣ ፷፭፣ ፰፮፣ ፰፰፣ ፸፮፣ ፹፩፣ ፹፱፣ ፺፪፣ ፺፭፣ ፳፮፣ ፺፰፣ ፩፻፴፭፣ ፩፴፮፣ ፩፻፵፯፣ ፩፻፵፰፣ ፩፶፻

አንድ ኃጢአተኛ ከኃጢአቱ በንስሐ ተመልሶ የእግዚአብሔርን ይቅርታ የሚጠይቅበት
መዝሙር፦ ፮፣ ፴፩፣ ፴፯፣ ፶፣ ፹፭፣ ፳፻፩፣ ፳፻፪ ፣ ፩፵፪

ጭንቀት፣ፈተና፣ ውርደት፣ ሐዘን፣ ስደትና ጭቆና በሚያጋጥም ጊዜ
መዝሙር፡-፪፣ ፮፣ ፲፫፣ ፳፩፣ ፴፭፣ ፵፩፣ ፵፫፣ ፵፬፣ ፶፪ ፣ ፶፭ ፡ ፶፮፣ ፶፱፣ ፷፬፣ ፷፰፣ ፸፬፣ ፸፯፡፸፱፣ ፹፣ ፹፣ ፹፰፣ ፺፡፺፬፡፩፻፪፣ ፩፻፱፣ ፩፻፵፡፩፻፵፫

ፍርሃትና ፈተና ሲያጋጥም በእግዚአብሔር ለመተማመን
መዝሙር፦ ፲፩፣ ፲፮፣ ፲፰፣፳፣ ፳፭፣ ፳፯፣ ፳፰፣ ፴፣ ፴፪፣ ፴፯፣ ፵፮፣ ፶፬፣ ፶፯፣ ፷፪፣ ሮ፣ ፸፩፣ ፻፩፣ ፩፻፲፭፣ ፻፳፬፣ ፻፳፩፣ ፻፵፬፣ ፩፵፮

የእግዚአብሔር፣ ሕጉና ቤቱ በሚናፈቅበት ጊዜ
መዝሙር፡ ፲፮፣ ፲፯፣ ፲፰፣ ፣ ፵፩፣ ፵፬፣ ፷፫፣ ፸፪፣ ፹፫፣ ፩፻፲፱፣ ፩፻፳፩፣ ፩፻፴፩

ካህናት የቤተ መቅደስን ደረጃዎች ሲወጡ የሚዘምሩአቸው የመዓርግ መዝሙሮች
ከመዝሙር ፩፻፪ እስከ ፩፻፴፫

እነዚህ መዝሙሮቹ ለእግዚአብሔር ስምና ለጽድቁ ከተነሣ ታላቅ ቅንአትና ኀጠአትን፤ከፋትን ከመጥላት የተነሣ ጻድቅ ፍርዱን በማምጣት ከፉዎችን አዋርዶ ጻድቃንን ከፍ ከፍ እንዲየደርግ ምልጃን የሚያቀርቡ ናቸው።
መዝሙረ ዳዊት ከእግዚአብሔርና ከሰው ግንኙነት አኳያ ሲታይ የሰውን ሰሜት ና ፍላጎት በየደረጃው ከዳር እስከዳር እንደዚህ አድርጎ የገለጸ መጽሐፍ ነው ውዳሴና ተመስጦ ጥልቀት ባለው ሁኔታ ተገልጿል።የማይመች ሁኔታ ባጋጠመ ጊዜ ድንቅ የሆነ የእምነት ጸሎት ያቀርባል።መዝሙረ ዳዊት በሐዲስ ኪዳን ብዙ ጊዜና በተደጋጋሚ የተጠቀሰ መጽሐፍ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ የሚወደዱ መዝሙሮችን የያዘ መጽሐፍ ነው።
We are currently offering version 1.2. This is our latest, most optimized version. It is suitable for many different devices. Free download directly apk from the Google Play Store or other versions we're hosting. Moreover, you can download without registration and no login required.

We have more than 2000+ available devices for Samsung, Xiaomi, Huawei, Oppo, Vivo, Motorola, LG, Google, OnePlus, Sony, Tablet ... with so many options, it’s easy for you to choose games or software that fit your device.

It can come in handy if there are any country restrictions or any restrictions from the side of your device on the Google App Store.

What's New


Dark Mode feature added

Rate and review on Google Play store


4.7
3,614 total
5 88.2
4 3.9
3 3.9
2 1.0
1 3.0

Total number of ratings

Total number of active users rated for: መዝሙረ ዳዊት በግእዝ እና አማርኛ | PSALMS

Total number of installs (*estimated)

Estimation of total number of installs on Google Play, Approximated from number of ratings and install bounds achieved on Google Play.